ስለ ዳይሬክቶሬቱ
ኦዲት ዳይሬክቶሬት ሚ/ር መ/ቤቱ የተቋቋመበትን ዓላማና ግቦች ለማሳካት እንዲችልና የስጋት፣የቁጥጥርና የኮርፖሬት አስተዳደሩን ሂደት ውጤታማነትን ለመገምገምና ለማሻሻል የሚያግዝና ድጋፍ የሚሰጥ የሥራ ክፍል ነው፡፡ ዳይሬክቶሬቱ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የፋይናንስ፤ የህጋዊነትና የፐርፎርማንስ ኦዲትን ማሳደግ፣ የኦዲት ሥራዎችን ጥራትና ቅልጥፍና ማሻሻል፣ ወደ ግል ባለሀብት የሚዛወሩ የልማት ድርጅቶችን የርክክብ ሥራ በላቀ ሁኔታ በማስፈፀም የመንግሥትን ጥቅም በተሻለ የማስጠበቅና የሥራ ክፍሎች ዕቅዶች፣የመ/ቤቱ ህጎች ደንቦችና መመሪያዎች ተግባራዊነት፣ የሃብትና የንብረት አጠቃቀሞችን ተገቢነት የማረጋገጥ ተግባራትን በዋናነት ያከናውናል፡፡