.
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 55.55 ቢሊዮን አተረፉ፣
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2012 በጀት ዓመት ብር 122.14 ቢሊዮን ገቢ አገኘ::
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በጸጥታ ችግር ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረጉ
የመንግሥት የትራንፖርት ድርጅቶች በ2012 በጀት ግማሽ ዓመት ከታክስ በፊት ብር 9.05 ቢሊዮን አተረፉ
የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች በ2012 በጀት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከታክስ በፊት ብር 10.7 ቢሊዮን አተረፉ
በግብርና እና አግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ሁለት ኮርፖሬሽኖች የግማሽ በጀት ዓመት አፈጻጸም ተገመገመ
የኤጀንሲው አመራሮች የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በማኑፋክቸሪነግ ዘርፍ የተሰማሩ አምስት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 174 ሚሊዮን አተረፉ
በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በንግድና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ አራት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 77.6 ሚሊዮን አተረፉ
በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ብር 52.3 ቢሊዮን አተረፉ
ክቡር አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
Web Content Display
Web Content Display
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የክቡር አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል መልዕክት
በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 445/2011 ተቋቁሞ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በስሩ በተለያዩ የኢኮኖሚ መስኮች የተሰማሩ 21 ተጠሪ የልማት ድርጅቶች አሉት፡፡
ኤጀንሲው እነዚህን ድርጅቶች ውጤታማ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና ፋይናንስ ሥርዓት የመዘርጋት፣ አመራርና አስተዳደራቸውን የመከታተል፣ በልማት ድርጅቶቹና አክሲዮን ማኅበራቱ ውስጥ መንግሥት ያለውን የባለቤትነት መብት የማስጠበቅ፣ በመንግሥት ልማት ፖሊሲ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስምሪት መካከል የሚኖረውን ቅንጅት የማሳለጥ እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አስተዳደር የመንግሥት የባለቤትነት፣ የተቆጣጣሪ እና የፖሊሲ አውጪውን አካላት ኃላፊነትና ሚና በለየ መልኩ መተግበሩን የማረጋገጥ ዋና ዋና ዓላማዎችንና ከእነዚሁ ጋር የተያያዙ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች እንዲያከናውን የተቋቋመ ነው፡፡
በመሆኑም ለኤጀንሲው የተሰጡትን ዓላማዎች እና ኃላፊነቶች ለማሳካት ባለፉት ሁለት ዓመታት በለውጥ(Reform) ሥራዎችም ሆነ በኦፕሬሽን በርካታ ተግባራትን አቅዶ ፈጽሟል፡፡ አበረታች ውጤቶችንም አስመዝገቧል፡፡ በለውጥ ሥራ ረገድ ኤጀንሲውን ደረጃ በደረጃ ወደ የመንግሥት ይዞታ ኩባንያ (Government Holding Company) ለማሸጋገር ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመዳሰስ ባዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ላይ የአሠራር ሥርዓቶችንና የውስጥ አቅምን ለመገንባት ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቷል፡፡ በዚሁ መሠረት የፖርትፎሊዮ ሥራ አመራር፣የልማት ድርጅቶች ሥራ አመራር፣ የኤጀንሲ ተቋማዊ ሥራ አመራር፣ አስቻይ ሁኔታዎች እና አስተዳደር የሚሉ ዋና ዋና ተግባራት (Work streams) እና 16 እርምጃዎችን(Initiatives) ለይቶ ሠፊ ሥራ አከናውኗል፤ እያከናወነም ይገኛል፡፡
ከተከናወኑ ተግባራት መካከል በልዩ ልዩ ርዕሶች ለኤጀንሲውና ለልማት ድርጅቶች አመራሮችና ሠራተኞች ሥልጠናዎች መሰጠታቸው፣ የኮርፖሬት አስተዳደርና ፋይናንስ ሥርዓትን የተመለከቱ የተለያዩ መመሪያዎች ተዘጋጅተው ሥራ ላይ እንዲዉሉ መደረጉ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በኦፕሬሽንም ረገድ የልማት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ ትርፋማነት፣ ተወዳዳሪነት እና ወጪ ቆጣቢነት ላይ አተኩረው እንዲሰሩ ለማስቻል በተደረገው ጥረት አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል፡፡
እኔ ኤጀንሲውን በዋና ዳይሬክተርነት እንድመራ ከፍተኛ ኃላፊነት የተሰጠኝ እነዚህ በባለፉት ዓመታት የተጀመሩ የጋራ ጥረቶቻችንንና የተገኙ ውጤቶቻችንን ይበልጥ በማጠናከርና የልማት ድርጅቶች በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሆነው የሀገርን ኢኮኖሚ መደገፍ እንዲችሉ ለማብቃት ነው፡፡
ስለዚህ የኤጀንሲውና የተጠሪ የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ሠራተኞች ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት በየፊናችን እያደረግን ያለነው ርብርብ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ከዚህ አኳያ የመላው የሀገራችን ህዝብ እና የደንበኛና የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ተሳትፎና ድጋፍም ወሳኝ እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን፡፡ ለጋራ ዓላማችንም ስኬት ሁላችሁም ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ክብር እንዳለን እና ለመሻሻል ሁል ጊዜም ትኩረት ሰጥተን እንደምንሰራ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡